በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ የተሰራ ዶክመንታሪ ፊልም
ዜና
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ቅድመ መከላከል ስራዎች ዙሪያ ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ፡፡
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የእንስሳትን ጤንነት ለመጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱና ዋነኛው ካሌንደርን መሰረት ያደረገ የቅድመ መከላከል ስራ ነው፡፡
ጽ/ቤቱ በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው 5 ዞኖች ስር ለሚገኙ 1ዐ ወረዳዎች 2ዐዐ ለሚሆኑ የቀበሌ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በቅድመ መከላል ስራዎች ዙሪያ ከዚህ በፊት የተሰጠውን ስልጠና መሬት ለማስነካት እና ተግባሩ በሚፈፀምበት አሰራር ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር የወረዳ አስተዳዳሪዎች የዘርፉ የዞን የወረዳ ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡
ዜና
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የ2014 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ ፡፡
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የሚመለከታቸው የክልል እና የፕሮጀክቱ ወረዳ የስራ ሃላፊዎችና ሙያተኞች በተገኙበት የፕሮጀክቱን የ2014 በጀት ዓመት የዋና ዋና ስራዎችን አፈፃፀም ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ፡፡
የፕሮጀክቱ የዋና ዋና ስራዎችን አፈጻጸም እና የ2015 እቅድ በፕሮጀክቱ Monitering and Evalation ባለሙያ በሆኑት በአቶ እንደሻው ቀርቧል ፡፡
በቀረበው ሪፖርትም ፡-
- የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎች
- 33 መሰረታዊ የህብረት ስራን ከማደራጀትና መደገፍ አንጻር የተሰሩ ስራዎች
- የተቋማትን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ መሰረተልማት ከማሟላት ፣ ግብአት ከማቅረብ እና የባለሙያዎችን አቅም ከማሳደግ አንጻር የተሰሩ ስራዎች በሪፖርቱ በዝርዝር ቀርበዋል ፡፡
- በቀረበው ሪፖርትም ተሳታፊዎች ሰፊ ጊዜ ወስደው ተወያይተዋል ፡፡ በውይይቱም ፕሮጀክቱ በ3ቱ ኮምፖነንቶች እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን የሚበረታቱ እና ወደፊትም ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው መሆኑን በስፋት ተነስቷል ፡፡ እንደችግር እና መስተካከል ያለበት በርካታ የጋራፍላጎት ቡድኖች ወደ መስረታዊ ህብረት ስራ በማምጣት በኩል የተሰሩ ስራዎች ስራ አናሳ መሆኑን ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ የመጡትንም በሚፈለገው ጊዜ በተገቢው መልኩ ደግፎ ወደ ስራ ፈጥነው እንዲገቡ በማድረግ በኩል የተሰራው ስራ አናሳ መሆኑን ተገምግሟል ፡፡
ዜና
ክልላዊ የወተት ቀን በዓል ተከበረ
የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ጽ/ቤት በምዕ/አማራ ክልል፣ የዞን እና የማዕከላት የዘርፉ ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደንግላ ከተማ የወተት ቀን በአልን አክብሯል፡፡
ኘሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ ዶ/ር ጋሻው ሙጨ ሲሆኑ ሀላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው ክልላችን ሰፊ የሆነ የእንስሳት ሃብት ክምችት ያለው መሆኑን እና ይህንን ሃብትም ለማልማትና በአግባቡ ለመጠቀም በመሰረታዊነት በእንስሳት መኖ ልማትና ስነ-አመጋገብን ማሻሻል፣ በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እንዲሁም በእንስሳት ጤና አጠባበቅ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተሰሩ ስራዎችን ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል
ዜና
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማ ፕሮጀክት ከጋራ ፍላጎት ቡድን ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ያደጉ ማህበራትን አፈጻጸም ገመገመ ፡፡
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማ ፕሮጀክት በ2011 በጀት አመት በክልሉ በ15 ወረዳዎች በ4 የእሴት ሰንሰለት ለመስራት ወደ ተግባር ስራ የገባ ሲሆን ፕሮጀክቱ እስከ 2014 በጀት አመት 2700 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች 36851 አባላትን በቀይ ስጋ ፣ በወተት ፣ በዶሮ እና በዓሳ ተጠቃሚዎችን አደራጅቶ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል ፡፡ ከእነዚህ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች አሁን ላይ 82 ህብረት ስራ ማህበራት 5839 ተጠቃሚዎችን በማቀፍ በ4ቱ የእሴት ሰንሰለቶች ተደራጅተው ወደ ስራ ገብተዋል ፡፡
ፕሮጀክቱ የህብረት ስራ ማህበራትን አፈጻጸም ለመገምገም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ4/11/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የግምገማ መድረክ አካሄዷል ፡፡
የሀዘን መግለጫ
የመስሪያ ቤታችን ባልደረባ በሆኑት በወ/ሮ መለሰች መርሻ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን!
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ መለሰች መርሻ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
ቅንና በባልደረቦቻቸው ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት ወ/ሮ መለሰች መርሻ በመስሪያቤቱ ውስጥ በኤክስኪዩቲቭ ሴክሪታሪነት ያገለግሉ ሲሆን በሥራቸው ታታሪና ትጉህ እንዲሁም ሰው አክባሪ ሰራተኛ ነበሩ፡፡
ወ/ሮ መለሰች መርሻ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ለህክምና ቢወሰዱም በነበረባቸው የልብ ህመም ምክንያት ሊሻላቸው ባለመቻሉ በህክምና ላይ እንዳሉ ሰኔ 22/2014 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የቀብር ስነ ስርዓቱም በዛሬው እለት(በ23/10/2014 ዓ.ም) ማሪያም ቤተክርስቲያን ( በመርጡለ ማርያም ከተማ) ይፈፀማል
በወ/ሮ መለሰች መርሻ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቿ ፣ ለሥራ ባልደረቦቿ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን እንመኛለን፡፡
ነፍስ ይማር
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት
ዜና
የአብክመ ህብረት ስራ ማደራጃ ባለስልጣን ከክልሉ እንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በእንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ፕሮጀክት ድጋፍ በቀይ ስጋ፣በወተት፣በዶሮ እና በአሳ ሀብት ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን እና መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራትን ከማደራጀት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ የሁለቱ ተቋማት ሰራተኞች በተገኙበት ገመገሙ።
መድረኩን የከፈቱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ ወልደተንሳይ ሲሆኑ ሀላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው የእንሰሳት ሃብት ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልፀው በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማደራጀት እና የድጋፍ እና ክትትል የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይሰራል ብለዋል። ለዚህም ሁሉም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።
የእንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ፅፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ዶር ጋሻው ሙጨ በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በዚህ መልኩ ስራ በጋራ መገምገማቸው ጥንካሬዎችና እጥረቶችን ለይቶ በቀጣይ ስራን ቆጥሮ በመከፋፈል ወደ ስራ ለመግባት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል። ሀላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ መድረኮች እየተፈጠሩ ስራን በጋራ የመገምገም ስራ ይሰራል ብለዋል።
- የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት በታቀፉ ወረዳዎች ለሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ፡፡
- የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት በታቀፉ ወረዳዎች ለሚገኙ የመንግስትና የግል እንስሳት ጤና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡
- በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለወረዳና ለቀበሌ የእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች በደሴ ከተማ ስልጠና ተሰጠ ።
- በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለወረዳና ለቀበሌ የእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ ።