ዜና
በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለወረዳና ለቀበሌ የእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች በደሴ ከተማ ስልጠና ተሰጠ
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከአለም ምግብና እርሻ ድርጅት(FAO) ባገኘው የበጀት ድጋፍ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አራት ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ ስድሰት ወረዳዎች መቄት ፣ ታች ጋይንት ፣ ሰቆጣ ዙሪያ ፣ አምባሰል ፣ ወረባቡ እና ተሁለደሬ ወረዳ የሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችን ለአምስት ተከታታይ ቀናት በደሴ ከተማ ስልጠና ተሰጠ ።
ስልጠናውን የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ተሰማ በእንስሳት ጤና ላይ እየተሰሩ የነበሩ ስራዎች በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ በመሆኑ የበሽታ ፍንዳታዎች እየተከሰቱ ስለሆነ የእንስሳት ጤና ባለሙያውን ስልጠና በመስጠት እና የግብዓት አቅርቦት በመስጠት ክትባቶች በዘመቻ መልኩ ለመስጠት የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል ።
ዜና
ሃገር አቀፍ የንቦች ቀን ግንቦት 12 በባህር ዳር ከተማ ተከበረ
በኢትዩጽያ ከ10-12 ሚሊዩን ህብረ ንቦች እንዳሉ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ከዚህ ሀብት ከ500000 ቶን ማር እና ከ50000 ቶን በላይ ሰም ምርት ማምርት እንደሚቻል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይሁን እንጅ አሁን ላይ እየተመረተ ያለው ከ53000 ቶን በላይ ማርና ከ3800 ቶን ያልበለጠ የሰም ምርት ነው፡፡ ከአለን አቅም አንፃር ሲታይ የሚመረተውምርት ከ10% አይበልጥም ፡፡ ያም ሁኖ በአፍሪካ ከሚመረተው የማር ምርት 27% ከኢትዮጵያ ይሸፍናል፡፡ ከዓለም ደግሞ 2.7% የማር ምርት ድርሻ በማበርከት ከዓለም 10 ደረጃ ትገኛለች፡፡ በሰም ምርትም ከዓለም በ4ኛ ደረጃ በአፍሪካ 1ኛ ደረጃ ትገኛለች ፡፡ ወደ ክልላችን ስንመጣ በአማራ ክልል ከ1.3ሚ ያላነሰ ህብረ ንብ ይገኛል፡፡ ከዚህ ሃብት በዓመት እስከ 4ዐ000 ቶን የማር ምርት 4ዐዐ ቶን የሰም ምርት ማምረት ቢቻልም አሁን እየተመረተ ያለው 25000 ቶን ማር 1800 ቶን ሰም ነው፡፡ ይህም ከሃገር አቀፍ ድርሻው 20% ሲሆን ከአለን እምቅ ሃብት አንፃር ሲታይ አነስተኛ ነው፡፡ የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ይህንን ሃብት በተገቢው መልኩ አልምቶ የማርና የሰም ምርትን በጥራትና በብዛት ለማምረት ንብ አናቢውን በስልጠና፣ ዘመናዊ የማነቢያ ግብዓቶችን በማቅረብና የድጋፍና ክትትል ስራ የመስራት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡ በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘርፉ አበረታች ውጤቶች መመዝገብ ጀምረዋል፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት በ28/07/2014 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ፡፡ በንቅናቄ መድረኩ የፊደራል የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ቢሮ ኃላፊዎችና ም/ኃላፊዎች፣ ዩኒቨረስቲዎች፣ የምርምር ተቋማት እና የዞንና ወረዳ የዘርፍ ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
መድረኩን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ኃይለማሪያም ከፍያለው ሲሆን ሀላፊው በመልዕክታቸው ክልሉ ሰፊ የሆነ እንስሳት ሀብት ክምችት ያለው መሆኑን ገልጸው ይህን ሀብት ለማልማት በየደረጃው ያለው የዘርፍ አመራርና ሙያተኞች ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት እንደ ግብርና ቢሮም ይህን ዘርፍ በልዩ ሁኔታ ለመደገፍ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ዜና
የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ጥበቃ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አጋር ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
በመድረኩም ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ የአካባቢና ማህበረሰብ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ የወረዳ እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪና ባለሙያዎች እንዲሁም የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሰራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ከጥር 05/2014 ዓም በእንጀባራ ከተማ ተካሄደ፡፡ የመወያያ ጽሁፎች የኘሮጀክቱ የአካባቢና ማህበረሰብ ደህንነት ባለሙያ በሆኑ በአቶ ሀሰን ሙሀባው ሰፋ ያለ የመወያያ ጽሁፎች አቅርበዋል፡፡
ዜና
አሸባሪው ህውሓት በኮምቦልቻ ዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ላይ ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ በቆየባቸው ጊዜያት የኮምቦልቻ ዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝን ዘርፏል ንብረቶችን አውድሟል በተሰራው ጊዜያዊ ግምትም ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች ወድመዋል ፡፡
ü ለዶሮ እርባታ አገልግሎት የሚውሉ ከ15067 በላይ የእርባታ ዶሮዎች ታርደው ተበልቷዋል
ü ለእርባታ አገልግሎት የሚውል ከ100ሽህ በላይ የዶሮ እንቁላል ተበልቷል መብላት ያልቻሉትን አውድመውታል
ü ከ 12000 በላይ የእርቢ እጫጭቶችን ገሏል
ü 1 ትልቅ ጀነሬተር እና 2 ትራክተሮችን አውድሟል
ዜና
በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘረፋና ወድመት ደርሶበታል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን በቆየባቸው ጊዜያት የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ ዘርፏል ፣ ንብረቶችን አውድሟል
በምስራቅ አማራ ላሉ ወረዳዎች የእንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ስራዎችን ይጠቀምባቸው የነበሩ ንብረቶችን ዘርፈዋል ፣ አውደመዋል
የቢሮ መስኮትና በሮች ተሰባብረዋል ፣ ኮምፒውተሮች እና ማይክሮስኮፖች ወድመዋል ፣ የተለያዩ የእንስሳት መድሐኒቶች እና መሳሪያዎች ተዘርፈዋል መውሰድ ያልቻሉትን አውደመውታል፡፡
ዜና
በሰሜን ሽዋ ዞን የሚገኘው የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘረፋና ወድመት ደርሶበታል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሰሜን ሽዋ ዞን በቆየባቸው ጊዜያት የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከልን ዘርፏል ፣ ንብረቶችን አውድሟል
አሸባሪው ቡድን በዞኑ በቆየባቸው ጊዜ ካወደማቸውና ከዘረፋቸው ተቋማት መካከል አንዱ የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ነው፡፡ ለዝርያ ማሻሻያ የሚውሉ በጎችን አርደው በልተዋል ፣ የበጎች መጠለያና ቢሮዎችን አቃጥለዋል ፣ ኮምፒውተሮች ፣ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና የበጎች መኖ ጨምሮ በርከት ያሉ ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውሉ ንብረቶች በአሸባሪው ቡድን ተዘርፈዋል ፣ መውስድ ያልቻሉትን አቃጥለውታል፡፡