ዜና
በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘረፋና ወድመት ደርሶበታል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን በቆየባቸው ጊዜያት የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ ዘርፏል ፣ ንብረቶችን አውድሟል
በምስራቅ አማራ ላሉ ወረዳዎች የእንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ስራዎችን ይጠቀምባቸው የነበሩ ንብረቶችን ዘርፈዋል ፣ አውደመዋል
የቢሮ መስኮትና በሮች ተሰባብረዋል ፣ ኮምፒውተሮች እና ማይክሮስኮፖች ወድመዋል ፣ የተለያዩ የእንስሳት መድሐኒቶች እና መሳሪያዎች ተዘርፈዋል መውሰድ ያልቻሉትን አውደመውታል፡፡
ዜና
በሰሜን ሽዋ ዞን የሚገኘው የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘረፋና ወድመት ደርሶበታል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሰሜን ሽዋ ዞን በቆየባቸው ጊዜያት የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከልን ዘርፏል ፣ ንብረቶችን አውድሟል
አሸባሪው ቡድን በዞኑ በቆየባቸው ጊዜ ካወደማቸውና ከዘረፋቸው ተቋማት መካከል አንዱ የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ነው፡፡ ለዝርያ ማሻሻያ የሚውሉ በጎችን አርደው በልተዋል ፣ የበጎች መጠለያና ቢሮዎችን አቃጥለዋል ፣ ኮምፒውተሮች ፣ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና የበጎች መኖ ጨምሮ በርከት ያሉ ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውሉ ንብረቶች በአሸባሪው ቡድን ተዘርፈዋል ፣ መውስድ ያልቻሉትን አቃጥለውታል፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ከአጋር ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ
እንስሳና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በ2012 እና በ2013 በደረጃ አንድ ከ10 እስከ 25 አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን በጋራ ፍላጎት ቡድን በማደራጀት የአመራረት ስረዓትን በማሻሻል ከእጅ ወደ አፍ ሲመረት የነበረዉን ትርፍ ምርት በማምረት ለገበያ ታሳቢ አድርጎ መስራትን ለማለማመድ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ በፕሮጀክቱ አሰራር መሰረት በደረጃ አንድ ድጋፍ የተደረገላቸውን በጋራ የማምረት ልምዳቸውን ለማዳበርና የገበያ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ወደ 31 ህብረት ስራ ማህበራት የማሳደግ ስራ በ2013 ተሰርቷል፡፡ በመሆኑም በ2013 በተሰራው ስራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት በ2014 ዓ/ም በአዲስ ለማደራጀት የህብረት ስራ ኮሚሽን ተቋምን እና የእንስሳት ጽ/ቤት ተቋም ጋር የምክክር መድረክ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
ዜና
በአማራ ክልል በተመረጡ አምስት ወረዳዎች የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የዝርያ ማሻሻል ስራን በክልሉ ተደራሽና ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንስት ጥጃ ብቻ የሚያስወልድ ሴክሲድ ሴመን የተባለውን አዲስ ቴክኖሎጅ በተመረጡ አምስት ወረዳዎች አስጀመረ፡፡ ሴክሲድ ሴመን ማለት በሠው ሠራሽ ማዳቀል ዘዴ እንስት ጥጃን ከ80-90% ማስገኘት የሚችል አባላዘር ማለት ነው ፡፡ ሴክሲድ ሴመን ከመደበኛ አባላዘር የሚለየው በአስተማማኝ ደረጃ ከ80-90% ማስወለድ መቻሉ ሲሆን መደበኛ አባላዘር ግን 50% እንስት እና 50% ተባዕት ጥጃ ሊያስገኝ የሚችል አባላዘር ሲሆን ሴክሲድ ሴመን በመጠቀም የዝርያ ማሻሻል ሥራን በማፋጠን በርካታ ቁጥር ያላቸውን እንስት ጥጆች ፤ጊደሮችና ላሞች ማስገኘት መቻሉ ነው፡፡ የሴክሲድ ሴመን አጠቃቀምን ውጤታማ ለማድረግ የሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ የእርባታ ወቅት ፤የወሊድ መጠን ፤የድቀላ አገልግሎት ብዛት ፤የአካባቢው ሁኔታ ፤የእርባታ መንጋ ቁጥር ፤የሚመረት የወተት መጠን መረጃ በማየት ይከናወናል፡፡
ዜና
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ EAAP በተባለ ኘሮጀክት በክልሉ በሚገኙ 6 ወረዳዎች ለ6 ኢንተርኘራይዞችን ለእያንዳንዱ 1.4 ሚሊዮን ብር ደጋፍ ተደረገ ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የክልሉን የንብ ሀብት ልማት ለማዘመን እና አናቢውን ተጠቃሚ ለማድረግ በስልጠና፣ በግብዓት አቅርቦትና ድጋፍና ክትትል በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተሰሩ ስራዎችም አበረታች ውጤቶች ተመዝገበዋል፡፡ ጽ/ቤቱ የሚሰራቸው ስራዎች በመደገፍ ኘሮጀክቶች ትልቅ ፋይዳ አላቸው፡፡ከነዚህ ኘሮጀክቶች ውስጥ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ EAAP የተባለ ኘሮጀክት በክልሉ በሚገኙ 6 ወረዳዎች 6 ኢንተርኘራይዞችን ለእያንዳንዱ 1.4 ሚሊዮን ብር በመደገፍ በስልጠና በግብዓት አቅርቦትና መሠረተ ልማቶችን በማሞላት የንብ ሀብት ልማትን ለማዘመን የሚሰራውን ስራ ሲደግፉ ቆይተዋል፡፡ ኘሮጀክቱ የማጠቃለያ ስራ ርክክብ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ 29/03/2014 በዳንግላ ከተማ የመስክ ጉብኝት እንዲሁም በ 30/03/2014 በባህር ዳር ከተማ ኘሮጀክቱ በቆይታው የሰራቸው ስራዎችና በቀጣይ እንዴት ማስቀጠል እንደሚገባ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡ በምክክር መድረኩ የተገኙ ተጠቃሚዎችና ባለድርሻ አካላትም በቀጣይ ስራውን ለማስቀጠል በሚችሉበት ሁኔታ በስፋት ተወያይተው የጋራ መግባባት በማድረግ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
ዜና
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከልን ጎበኙ
ዜና
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሃይለማርያም ከፍያለው የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽቤት ሃላፊ ዶር ጋሻው ሙጨ በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እና የመስክ ምልከታ ላይ የሰጡት አስተያየት
- በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት የደብረ ዘይት ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዮት የእንስሳት ስነ-ተዋልዶ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ ታምራት ደገፋ በማዕከሉ ተገኝተው የሰጡት አስተያየት
- የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል ሃላፊ አቶ ፈንታሁን ዳኛው በማዕከሉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አስመልክቱ የሰጡት ማብራሪያ
- በ24/03/2014 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስተዋወቅ
- የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በእንስሳት ዘርፍ የተሰማሩ የኒዬኖችን በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ