ዜና
የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት በ 20/06/2013 ዓም በእንጅባራ ከተማ የ6 ወሩን የኘሮጀክት አፈፃፀም በቴክኒክ ኮሚቴው ተገመገመ፡፡
የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት በ 20/06/2013 ዓም በእንጅባራ ከተማ የ6 ወሩን የኘሮጀክት አፈፃፀም በቴክኒክ ኮሚቴው ገመገመ፡፡ የኘሮክቱ የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም በኘሮጀክቱ በኩል ከቀረበ በኃላ ከቤቱ በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ በስፋት ተወያያቶ የሚከተሉትን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡
ዜና
ከአሁን በፊት በቆሎ እና ዳጉሳ ይዘሩበት የነበረውን ማሳቸውን የተሻሻለ የእንስሳት መኖ በመዝራት በወተት ሃብት ልማት ስራ ተጠቃሚ የሆኑት አርሶ አደር ተሾመ መለስ
በምዕራብ ጎጃም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ አብችክሊ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ተሾመ መለስ ከአሁን በፊት በቆሎና ዳጉሳ ይዘሩት የነበረውን ማሳቸውን እንዲሁም ከግለሰቦች የማሳ መሬቶችን በመከራየት በ1.5 ሄክታር የተሻሻለ የእንስሳት መኖ በመዝራት በ2008ዓ.ም በወተት ሃብት ልማት ስራ የገቡ ሲሆን አርሶ አደሩ አሁን ላይ 7 የወተት ላሞች እና 5 ጥጆች ያሎቸው ሲሆን በቀን ከ52 ሊትር በላይ ወተት እንደሚያገኙ ገልጸውልናል ፡፡
ዜና
የፌደራል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ እና የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ዙሪያ የሰጡት አስተያየት ፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ ከጥር 17-21/2013 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲያካሄድ፡፡በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ተካፋይ የነበሩት ከአማራ ክልል ህብረት ስራ ኤጀንሲ እና ከአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የመጡ ባለሙያዎች እና የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የወረዳ አስተባባሪዎች በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ዙሪያ የሰጡት አስተያየት
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲያካሄድ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ
1 በገቨርናንስና ንዑስ ፕሮጀክት አዘገጃጀት
2 በአካባቢ እና ማህበራዊ ደህንነት ጉዳይ
3 በግብይት ሰንሰለት ዙሪያ ከጥር 17-21/2013 በእንጅባራ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና አካሄደ፡፡
ዜና
በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚሰራቸው በርካታ ስራዎች ውስጥ ወጣቶች በዘርፉ በስፋት ተደራጀተው እንዲገቡ እና የተሻለ አሰራር ተከትለው እንዲሰሩ ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡ በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡ኢንተርኘራይዙ የሚገኝው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ላስታ ገራዶ 04 ቀበሌ ሲሆን ስራ የጀመረው በ2007 ዓም በ 5 ላሞች ነው፡፡
ዜና
በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ከአረብ ሃገር ተመልሰው በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተደራጁት ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይ በ2009 ዓም 1000 ጫጩቶችን በመያዝ ስራ የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ በዓመት ከ20,000 ያላነሱ ጫጩቶችን በማሳደግ ለተጠቃሚዎች ያቀርባሉ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ህ/ሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከስራቸው ስራዎች አንዱ የተሻለ የእንቁላል እና የስጋ መጠን የሚሰጡ የዶሮ ዝርያዎችን በግብዓት አቅራቢዎች አማካኝነት ለህብረተሰብ እንዲዳረስ እና ሳይንሳዊ አሰራሩን ተከተለው እንዲሰሩ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡ ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይዝ የሚገኝው በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ሲሆን ኢንተርኘራይዙ በ2009 ዓም 1000 ጫጩቶችን በማሳደግ ስራ የጀመረ ሲሆን
ዜና
በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከአረብ ሃገር ተመልሳ በወተት ሃብት ልማት ስራ የተሰማራችው ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን በ2010 ዓ.ም 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገባች ሲሆን አሁን ላይ በቀን ከ650 ብር ያላነሰ ከወተት ሽያጭ ታገኛለች፡፡
የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በውስን ካፓታል እና መሬት ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ ነው፡፡ በዘርፉ በርካታ ወጣቶች እና ሴቶች ወደ ስራ በመግባት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ወጣቶችና ሴቶች መካከለ ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን አንዳ ናት፡፡ ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን ነዋሪነቷ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ሲሆን ግለሰቧ የወተት ሀብት ልማት ስራ የጀመረችው በ2010 ዓም ነው፡፡ አሁን ላይ 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ እና ባላት ውስን ቦታ የተሻሻሉ የመኖ ልማቶችን በማልማትና