ዜና
በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በወተት ሃብት ልማት ስራ የተሰማራው ወጣት ናስር ሙህመድ 9 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራው ገብቶል
የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በውስን ካፓታል እና መሬት ለወጣቶችና የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ ነው፡፡ በዘርፉ በርካታ ወጣቶች ወደ ስራ በመግባት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ወጣቶች መካከለ ናስር ሙህመድ አንዱ ነው ወጣት ናስር ሙህመድ ነዋሪነቱ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆን ግለሰቡ የወተት ሀብት ልማት ስራ የጀመረችው በ2010 ዓም ነው፡፡ አሁን ላይ 9 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራው በመግባት በመርሳ ከተማ የወተት ተዋፅኦዎችን ለአካባቢው ማህበረሰብ እያቀረበ ይገኛል በዚህን ተጠቃሚ መሆኑን ገልጾልናል፡፡
ዜና
በአዊ ብ/አ/ዞን በእንጅባራ ከተማ በወተት ሃብት ልማት ሰራ የተሰማሩት አለም የወተት ላም እርባታ 18 ላሞች፣ ጊደሮች እና ጥጆች በመያዝ በዘርፉ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል፡፡
በአማራ ክልል ከሚገኝ በርካታ የወተት ላም እርባታ ድርጅቶች አንዱ አለም የወተት ላም እርባታ ነው፡፡ የወተት ላም እርባታው የሚገኝው በአዊ ብ/አ/ዞን በእንጅባራ ከተማ ነው፡፡ የወተት ላም እርባታው በ 2003 ዓ.ም እንደጀመረ የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ የሽወርቅ ምህረት ገልፀውልናል፡፡የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ የሽወርቅ ምህረት አሁን ላይ በእርባታ ድርጅቱ ቁጥራቸው ከ 18 ያላነሱ ላሞች፣ ጊደሮች እና ጥጆች እንደሚገኙ ጠቁመው በቀን ከ 80 ሊትር ያላነሰ ወተት እንደሚያገኙና በዚህም ሂውታቸውን በተሻለ መልኩ እየመሩ እንደሆነ ገልፃዋል፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንሰሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከፋርም ሬዲዮ ጋር በመተባበር
በዶሮ እርባታ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በዶሮ ዙርያ አስተማሪ የሆኑ መልእክቶችን
በአማራ ሬዲዮ ዘወትር እሮብ ማታ ከ1፡20 እስከ 1፡50 እንዲሁም በድጋሜ እሁድ ከቀኑ
ከ11:20 እስከ 11:50 ያስተላልፋል።በመሆኑም ፕሮግራሙን በመከታተል አስተያየታችሁን
እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ዜና
በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች የስራ እንቅስቃሲ
የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰንቶ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የተሻለ የእንቁላል ምርትና ስጋ መስጠት የሚችሉ የውጭ ደም ያላቸው የዶሮ ዝርያዎች ከ 1 ቀን ጫጩት አቅራቢ ካምፓኒዎች አሳዳጊዎች እየወሰዱ እንሚያሳደጉ አስፈላጊ ሙያዊ እገዛዎችን በቅድመ ዝግጅትና በተግባር ምዕራፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ኤጀንሲው በ2012 በጀት አመት በ 1 ቀን ጫጩት ማሳደግ ስራ በሰራ ላይ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው በኢንተርኘራይዝ የተደራጅ አሳዳጊዎች ቁጥር 2250 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 754 ሴቶች ናቸው፡፡
ዜና
እናትና ልጅ የወተት ላም እርባታ በ2ዐዐ2 ዓ/ም በጎንደር ከተማ በ2 የወተት ላሞች የተጀመረ ሲሆን አሁን ላይ ከ2ዐ በላይ የወተት ላሞች እንዲሁም 37 የሚሆኑ ጊደሮችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራ ገብተዋል፡፡
በክልላችን ከሚገኙ ዘመናዊ የወተት ላም እርባታ አንዱ እናትና ልጅ የወተተ ላም እርባታ ነው የወተት ላም እርባታ በ2ዐዐ2 ዓ/ም በጎንደር ከተማ በ2 የወተት ላሞች የተጀመረ ሲሆን አሁን ላይ ከ2ዐ በላይ የወተት ላሞች እንዲሁም 37 የሚሆኑ ጊደሮችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ ብርሃኔ ተዋበ እንደለፁልን ማህበሩ በቀን ከ15ዐ በላይ ወተት ለተጠቃሚ እንደሚያርቡ ጠቁመው ወተት የሚያቀርቡበት የራሱ የወተት መሸጫ ጣቢያ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ወ/ሮ ብርሃኔ ተዋበ አክለውም ከወተት ሽያጭ በተገኘ ገቢ ዘመናዊ ፎቅ እየገነቡ መሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ስራውን የበለጠ ለማስፋት ሃሣብ እንዳላቸው ገልፀል፡፡
ዜና
በእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ኘሮጀክት በዓሣ ሃብት ልማት የተደራጁ ወጣቶች እና በአርሶ አደሮች የዓሳ ኩሪ ጫጩት የመጨመር ስራ ተሰራ
የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በክልሉ የዓሣ ሃብት ልማትን ለማሣደግ እና ህብረተሰቡን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ከባ/ዳር የዓሣ ምርምር ማዕከል የዓሣ ጫጩት በማራባት በእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ኘሮጀክት በዓሣ ሃብት ልማት የተደራጁ ወጣቶች እና በአርሶ አደሮች የዓሳ ኩሪ ጫጩት የመጨመር ስራ ተሰራ
ዜና
በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 04 በወተት ሃብት ልማት ስራ ጥሩ እንቅስቃሲ እያደረጉ ያሉ ግለሰብ
አቶ እንድሪስ አደም ነዋሪነታቸው በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 04 ነዋሪ ሲሆኑ ግለሰቡ ከዚሀ በፊት የመንግስት ሰራተኛ የነበሩ ሲሆን ግለሰቡ ከ 2010 ዓ.ም ጀምሮ 5 የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን አሁን ላይ ጊደሮች እና ጥጃዎችን ጨምሮ ከ 30 ያላነሱ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸውን እንስሳት ይዘዋል፡፡ ግለሰቡ ለላሞቻቸው ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል እውቀትና እና የስራ ተነሳሽነት ያላቸው ሲሆን በባለሙያዎች ዘንድ የሚደረግላቸውን ድጋፍም በአግባቡ እንደሚተገብሩ የወተት ላም እርባታ ጣቢያቸውን በጐበኝንበት ወቅት ማረጋገጥ ችለናል፡፡
ዜና
በ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ሀርቡ 02 ቀበሌ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት የኘሮጀክት ድጋፍ በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች
- አቶ ጀማል አወል ነዋሪነታቸው በቃሉ ወረዳ ሀርቡ ቀበሌ ሲሆን ግለሰቡ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት 30 የእንቁላል ዶሮዎች፣ የመመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸው በዶሮ እርባታ ወደ ስራ የገቡ ግለሰብ ሲሆኑ ግለሰቡ ለዶሮዎች ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ በመቻላቸው በቀን 27 እንቁላል ያገኛሉ፡፡
- አቶ ጀማል የሱፍ ነዋሪነታቸው በቃሉ ወረዳ ሀርቡ ቀበሌ ሲሆን ግለሰቡ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት 30 የእንቁላል ዶሮዎች፣ የመመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸው በዶሮ እርባታ ወደ ስራ የገቡ ግለሰብ ሲሆኑ ግለሰቡ ለዶሮዎች ተገቢውን እንክብካቤ ባለማድረጋቸው በቀን ከ 17-20 እንቁላሎችን በአማካኝ ያገኛሉ፡፡
- የአማራ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከብሄራዊ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ማአከል ጋር በመተባበር ከታህሳስ 3—12/04/2013 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት ማአከል ቁጥራቸዉ 48 ለሚሆኑ የአዳቃይ ቴክኒሻን ባለሙያዎች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጠ ፡፡
- የአብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከicipe Moyeshe ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከታህሳስ 3__4/2013 በባህርዳር ከተማ የማር ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ አካሄደ፡፡
- የደቡብ ጎንደር ዞን እንስሳት ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት የ2012 በጀት ዓመት ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 እቅድ ትውውቅ መድረክ
- የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2013 እቅድ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡