ዜና
በምስራቅ አማራ በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ በጋራ ፍላጎት ቡድን የተደራጅ ተጠቃሚዎችን ወደ ህብረት ስራ ማህበር ለማሳደግ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በምስራቅ አማራ ድጋፍ በሚያድረግባቸው ስድስት ወረዳዎች ደሴ ዙሪያ ወረዳ ፣ ቃሉ ወረዳ ፣ ጉባላፍቶ ወረዳ ፣ ዳዋጨፋ ወረዳ ፣ ሞረትና ጅሩ ወረዳ እና ባሶናወረና ወረዳ በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ተደራጁ ለሚገኙ 40 (አርባ) የህብረት ስራ ማህበር አባላትና አመራሮች ፣ የህብረት ስራ ማህበራት ገዥዎች ፣ የወረዳ ፕሮጅክት አሰተባባሪዎች ፣ የወረዳ እና የክልል የህብረት ስራ ማስፋፊያ ባለሙያዎች ፣ የእንስሳት እና ዓሳ ልማት ጽ/ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት የግንዛቤ ፍጠራ መድረክ አካሄደ፡፡
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች በደረጃ አንድ (በጋራ ፍላጎት ቡድን) ተደራጅተው ሲሰሩ የቆዩትን በአዲስ መልክ ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ እና በደረጃ አንድ ተጠቃሚ የነበሩትን ወደ ነባር ህብረት ስራ ማህበራት እንዲገቡ በማስቻል በ2015 ዓ/ም 112 ህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት በፕሮጀክቱ የተቀመጡትን መስፈርቶች በመከተልና በማወዳደር 70 የህብረት ስራ ማህበራትን ለእያንዳንዳቸው 1,580,000 ብር በድምሩ 110,600,000.00 ብር ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡:
ዜና
በምዕራብ አማራ በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ በጋራ ፍላጎት ቡድን የተደራጅተው ተጠቃሚዎችን ወደ ህብረት ስራ ማህበር ለማሳደግ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ ::
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ተደራጁ ለሚገኙ 67 (ስልሳ ሰባት) የህብረት ስራ ማህበር አባላትና አመራሮች ፣ የወረዳ እና የክልል የህብረት ስራ ማስፋፊያ ባለሙያዎች ፣ የእንስሳት እና ዓሳ ልማት ጽ/ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት የግንዛቤ ፍጠራ መድረክ አካሄደ፡፡
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች በደረጃ አንድ (በጋራ ፍላጎት ቡድን) ተደራጅተው ሲሰሩ የቆዩትን በአዲስ መልክ ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ እና በደረጃ አንድ ተጠቃሚ የነበሩትን ወደ ነባር ህብረት ስራ ማህበራት እንዲገቡ በማስቻል በ2015 ዓ/ም 112 ህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት በፕሮጀክቱ የተቀመጡትን መስፈርቶች በመከተልና በማወዳደር 70 የህብረት ስራ ማህበራትን ለእያንዳንዳቸው 1,580,000 ብር በድምሩ 110,600,000.00 ብር ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡
በምስራቅ አማራ ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ በመከላከል ረገድ የተሰሩ ሰራዎችን በተመለከተ ከአቶ ንጉሴ ተፈራ የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርመራ ዳይሬክተር ጋር የተደረገ ቆይታ
ዜና
በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ አውዘት ቀበሌ አለቅት ወንዝ ፍጋን ተብሎ የሚጠራው ተፋሰስ የለማ የውል የግጦሽ መሬት እና የዝርያ ማሻሻል ስራ ተጎበኘ ::
ዜና
የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል ስራ በተመለከተ የንቅናቂ መድረክ ተካሄደ ::
በዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል ስራዎቻችን ላይ ያተኮረ የንቅናቂ መድረክ የክልል፣ የዞን ስራ ሀላፊዎችና ቁጥራቸው 417 የሆኑ አዳቃይ ቴክኒሻኖች በተገኙበት ሀምሌ 1/2014ዓ.ም በደብረታቦር ከተማ ተካሄደ፡፡
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ዋና ዋና ስራዎች አንዱ እና ዋነኘው የዝርያ ማሻሻል ስራ ነው ፡፡
በ2015 በጀት ዓመት ከዝርያ ማሻሻል ስራ ጋር ተይዞ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በቅድመ ዝግጅት እንዲህ አይነት የንቅናቂ መድረክ መካሄዱ በ2014 በጀት ዓመት በአፈጻጸም ረገድ የነበሩ ውስንነቶችን በተገቢው መልኩ ለይቶ በቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያግዛል ፡፡
ዜና
የክልሉ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የወል ግጦሽ መሬቶችን ከልሎ በማልማት የተሻለ ተሞክሮ ባለው የምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ የልምድ ልውውጥ አካሄደ።
የክልሉ እንስሳት ና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የእንሰሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ስራዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛው የእንስሳት መኖ ልማትና ስነ አመጋገብን የማሻሻል ስራ ነው። መኖ የወተት፣የስጋ እና የእንቁላል ምርትን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ አለው።
ዜና
አራተኛውን ዙር የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ቁጥጥርና ማጥፋት ዘመቻ ተገመገመ፡፡
በመድረኩ የፊደራል ግብርና ሚኒስቴር ፣ከአጎራባች ክልል ከቤንሻጉል ጉምዝ ክልል እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ፣ከዩኒቨርስቲዎች ፣ የዞንና ወረዳ የሚመለከታቸው ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የክልል ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ እንደሚታወቀው በጎችና ፍየሎች ውሃ በሚጠጡበትና ለግጦሽ አብረው በሚውሉበት ጊዜ በትንፋሽ ስለሚተላለፍ በጎችንና ፍየሎችን በከፍተኛ ደረጃ በመግደል የሚታወቅ በሽታ ነው ፡፡
ይህን በሽታ ለመቆጣጠርና ለማጥፍት በአለም ደረጃ 2030 በኢትዩጽያ ደግሞ 2027 ለማጥፋት ትኩረት ተሰጥቶ በርካታ ስራዎች እንደ ሃገር እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ዜና
ታስክ ፎርሱ በ2014 በጀት አመት የበጎችና ፋየሎች ደስታ መሰል በሽታ በመከላከል እረገድ የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ።
የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ በጎችና ፍየሎችን በከፍተኛ ደረጃ የሚገድል በሽታ ነው። በሽታውን በአለም ደረጃ 2030 በኢትዪጰያ 2027 ለማጥፍት ግብ ተጥሎ በርካታ ስራዎች እንደ ሀገር እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል። እንደ ከልል የበጎችና ፋየሎች ደስታ መሰል በሽታን ለመከላከል በምእራብና ምስራቅ አማራ በሚገኙ ሁለቱ የእንስሳትጤና ላብራቶሪዎች በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል። በበጀት አመቱ የተሰሩ ስሪዎች አፈፃፀም ተግባሩን በበላይነት እየገመገመ ለሚመራው ታስክ ፎርስ ሁለቱ ላቦራቶሪዎች ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፓርቱ በሽታዉን ማህበረሰብ አሳታፊ በሆነ መልኩ ለመከላከል በግንዛቤፈጠራ፣በስልጠና እና በክትባት ዙሪያ የተሰሩ ሰራዎች ቀርበዋል። በቀረበዉ ሪፖርትም