ዜና
እድገት ለህብረት የንብ አናቢዎች ማህበር የሚገኘው በዋግ/ብ/አስ ዞን ሰቆጣ ወረዳ 03/ሃሙሲት ቀበሌ ሲሆን ማህበሩ ኡሁን ላይ ወንድ 7 ሴት 3 በድምሩ 10 አባላትን በመያዝ በ23 ዘመናዊ ቀፎዎች የንብ ማነብ ስራ እየሰሩ ይገኛል::
የአማራ ክልል ለንብ ሃብት ልማት ምቹ ሰነ-ምህዳር ያለው ክልል ነው ፡፡ እንደ ማዕከላዊ ስታስቲክስ 2017/2018 መረጃ መሰረት በክልሉ 1.15ሚሊዮን ያክል የንብ መንጋ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳ በክልላችን ሰፊ የሆነ የንብ ሃብት ልማት ቢኖርም ንብ አናቢው የህብረተሰብ ክፍል አሁንም ድረስ በሚከተለው ኋላቀር የንብ ማነብ ዘዴ ህብረተሰብ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ሳያገኝ ቆይቶል ፡፡ የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ንብ አናቢው የህብረተሰብ ክፍል ሳይንሳዊ ዘዴ ተጠቅሞ የንብ ማነብ ስራ እንዲሰራ በስልጠና ፤ በግብዓት አቅርቦትና በድጋፍና ክትትል በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛል ፡፡
ዜና
ጥምቀተ ባህር የንብ አናቢዎች ማህበር የሚገኘው በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ሹምሻ ቀበሌ ሲሆን ማህበሩ ኡሁን ላይ 8 አባላትን በመያዝ በ37 ዘመናዊ ቀፎዎች የንብ ማነብ ስራ እየሰሩ ይገኛል::
የአማራ ክልል ለንብ ሃብት ልማት ምቹ ሰነ-ምህዳር ያለው ክልል ነው ፡፡ እንደ ማዕከላዊ ስታስቲክስ 2017/2018 መረጃ መሰረት በክልሉ 1.15ሚሊዮን ያክል የንብ መንጋ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳ በክልላችን ሰፊ የሆነ የንብ ሃብት ልማት ቢኖርም ንብ አናቢው የህብረተሰብ ክፍል አሁንም ድረስ በሚከተለው ኃላ ቀር የንብ ማነብ ዘዴ ህብረተሰብ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ሳያገኝ ቆይቶል ፡፡ የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ንብ አናቢው የህብረተሰብ ክፍል ሳይንሳዊ ዘዴ ተጠቅሞ የንብ ማነብ ስራ እንዲሰራ በስልጠና ፤ በግብዓት አቅርቦትና በድጋፍና ክትትል በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛል ፡፡
ዜና
የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከሴፍ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በቀን 11/02/2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የወተት ቀን አከበረ፡፡
የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከሴፍ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በቀን 11/02/2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የወተት ቀን አከበረ፡፡ በበአሉ ጥሪ የተደረገላቸዉ የክልል፣የዞን እና የወረዳ ተሳቴፊዎች እና የዳንግላ ከተማ 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ በአሉን አስመልክቶ የፕሮጀክቱ ሀላፊ አቶ ደስታ ዳመና እንደገለጹት ሴፍ ፕሮጀክት በአማራ ክልል በ2 ዞኖች በምእራብ ጎጃምና በአዊ ብ/አ/ዞን በሚገኙ 4 ወረዳዎች የወተት ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ እና ገቢን በመጨመር በሴቶችና
የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ መልዕክት
የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በደንብ ቁጥር 81/2003 ዓ.ም በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት የተቋቋመ ሲሆን ክልላችን ለእንስሳት ሃብት ልማት ምቹ የሆነ የአየር ንብረት ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ 2015/2016 ጥናት በክልላችን 15454923 ዳልጋ ከብት 9797248 በግ 6085912 ፍየል 19958894 ደሮ 3478747 የጋማ ከብት 1328235 የንብ መንጋ 63500 የግመል ሀብት ያለ ቢሆንም በህ/ሰቡ ኋላቀር የሆነ የአረባብ ዘዴ ጋር ተያይዞ በሚስተዋሉ ምርታማ ያልሆኑ ዝርያዎች ቁጥር ላይ ብቻ አተኩሮ የመስራት፣ መኖን በተገቢው መልኩ አልምቶ በአግባቡ ያለመመገብ እንዲሁም የእንስሳትን ጤና በተገቢው መልኩ ከመጠበቅ አንጻር በሚስተዋሉ ችግሮች ምክንያት ህ/ሰቡም ሆነ ሀገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓት ቆይቷል፡፡