ዜና
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማ ፕሮጀክት ከጋራ ፍላጎት ቡድን ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ያደጉ ማህበራትን አፈጻጸም ገመገመ ፡፡
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማ ፕሮጀክት በ2011 በጀት አመት በክልሉ በ15 ወረዳዎች በ4 የእሴት ሰንሰለት ለመስራት ወደ ተግባር ስራ የገባ ሲሆን ፕሮጀክቱ እስከ 2014 በጀት አመት 2700 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች 36851 አባላትን በቀይ ስጋ ፣ በወተት ፣ በዶሮ እና በዓሳ ተጠቃሚዎችን አደራጅቶ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል ፡፡ ከእነዚህ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች አሁን ላይ 82 ህብረት ስራ ማህበራት 5839 ተጠቃሚዎችን በማቀፍ በ4ቱ የእሴት ሰንሰለቶች ተደራጅተው ወደ ስራ ገብተዋል ፡፡
ፕሮጀክቱ የህብረት ስራ ማህበራትን አፈጻጸም ለመገምገም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ4/11/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የግምገማ መድረክ አካሄዷል ፡፡
.jpg)
የሀዘን መግለጫ
የመስሪያ ቤታችን ባልደረባ በሆኑት በወ/ሮ መለሰች መርሻ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን!
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ መለሰች መርሻ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
ቅንና በባልደረቦቻቸው ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት ወ/ሮ መለሰች መርሻ በመስሪያቤቱ ውስጥ በኤክስኪዩቲቭ ሴክሪታሪነት ያገለግሉ ሲሆን በሥራቸው ታታሪና ትጉህ እንዲሁም ሰው አክባሪ ሰራተኛ ነበሩ፡፡
ወ/ሮ መለሰች መርሻ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ለህክምና ቢወሰዱም በነበረባቸው የልብ ህመም ምክንያት ሊሻላቸው ባለመቻሉ በህክምና ላይ እንዳሉ ሰኔ 22/2014 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የቀብር ስነ ስርዓቱም በዛሬው እለት(በ23/10/2014 ዓ.ም) ማሪያም ቤተክርስቲያን ( በመርጡለ ማርያም ከተማ) ይፈፀማል
በወ/ሮ መለሰች መርሻ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቿ ፣ ለሥራ ባልደረቦቿ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን እንመኛለን፡፡
ነፍስ ይማር
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት
ዜና
የአብክመ ህብረት ስራ ማደራጃ ባለስልጣን ከክልሉ እንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በእንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ፕሮጀክት ድጋፍ በቀይ ስጋ፣በወተት፣በዶሮ እና በአሳ ሀብት ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን እና መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራትን ከማደራጀት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ የሁለቱ ተቋማት ሰራተኞች በተገኙበት ገመገሙ።
መድረኩን የከፈቱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ ወልደተንሳይ ሲሆኑ ሀላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው የእንሰሳት ሃብት ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልፀው በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማደራጀት እና የድጋፍ እና ክትትል የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይሰራል ብለዋል። ለዚህም ሁሉም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።
የእንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ፅፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ዶር ጋሻው ሙጨ በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በዚህ መልኩ ስራ በጋራ መገምገማቸው ጥንካሬዎችና እጥረቶችን ለይቶ በቀጣይ ስራን ቆጥሮ በመከፋፈል ወደ ስራ ለመግባት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል። ሀላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ መድረኮች እየተፈጠሩ ስራን በጋራ የመገምገም ስራ ይሰራል ብለዋል።
ዜና
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት በታቀፉ ወረዳዎች ለሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው በምስራቅ አማራ ለሚገኙ ዞኖች ዋግኽምራ ብሔረሰብ ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ኦሮሞ ብሔረሰብ እና ሰሜን ሽዋ ዞን ለሚገኙ የዞንና እንስሳት ጤና ቡድን መሪዎች እና ለወረዳ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የዶሮ ፈንግል ክትባት(NEWCASTLE_DISEASE) አሠጣጥ ዙሪያ የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና በደሴ ከተማ ተሰጠ ።
የዕለቱን መድረክ የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሪክተር ዶ/ር ተምሩ ተሰማ የማህበረሰብ አቀፍ የዶሮ ፈንግል በሽታ አደገኛ የሆነ በሽታ በመሆኑ ሰልጣኞች የሚሰጣቸው የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና በመከታተልና በዶሮ ፈንግል ክትባት አሰጣጥ ዙሪያ በቂ እውቀት በመያዝ በየወረዳዎቻቸው ክትባት የሚሰጡ ሴቶች በመመልመል የወሰዱትን ስልጠና እንዴሰጡ አሳስበዋል ።
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት በታቀፉ ወረዳዎች ለሚገኙ የመንግስትና የግል እንስሳት ጤና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው በምስራቅ አማራ ለሚገኙ ዞኖች ዋግኽምራ ብሔረሰብ ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ኦሮሞ ብሔረሰብ እና ሰሜን ሽዋ ዞን ለሚገኙ የዞንና እንስሳት ጤና ባለሙያዎች እና ለወረዳ የእንስሳት ጤና ብድን መሪ ፣ ለመንግስት እንስሳት ጤና ባለሙያዎች እና ለግል የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በመንግስትና በግል የእንስሳት ጤና ተቋማት ጥምረት ላይ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና በግል እንስሳት ጤና ተቋማት ለመሰማራት የወጡ መመሪያዎችን በግልፅ አውቆ በቀጣይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት በጋራ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያግዝ ስልጠና በደሴ ከተማ ተሰጠ ፡፡
መድረኩን የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሮክቶሪት ዶ/ር ተምሩ ተሰማ የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በአስር አመት እቅዱ ላይ አሁን ያለውን 10% የሚሸፍነውን የግል የእንስሳት ጤና ተቋማት ለማሳደግ የግል የእንሳሳት ጤና ባለሙያዎችን በማበረታታትና አቅም በመገንባት በቀጣይ 10 ዓመት ውስጥ የግል የእንስሳት ጤና ተቋማትን ሽፋን 35% ለማድረስ አቅዶ እየሰራ ነው ፡፡
ዜና
በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለወረዳና ለቀበሌ የእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች በደሴ ከተማ ስልጠና ተሰጠ
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከአለም ምግብና እርሻ ድርጅት(FAO) ባገኘው የበጀት ድጋፍ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አራት ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ ስድሰት ወረዳዎች መቄት ፣ ታች ጋይንት ፣ ሰቆጣ ዙሪያ ፣ አምባሰል ፣ ወረባቡ እና ተሁለደሬ ወረዳ የሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችን ለአምስት ተከታታይ ቀናት በደሴ ከተማ ስልጠና ተሰጠ ።
ስልጠናውን የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ተሰማ በእንስሳት ጤና ላይ እየተሰሩ የነበሩ ስራዎች በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ በመሆኑ የበሽታ ፍንዳታዎች እየተከሰቱ ስለሆነ የእንስሳት ጤና ባለሙያውን ስልጠና በመስጠት እና የግብዓት አቅርቦት በመስጠት ክትባቶች በዘመቻ መልኩ ለመስጠት የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል ።