ዜና
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ EAAP በተባለ ኘሮጀክት በክልሉ በሚገኙ 6 ወረዳዎች ለ6 ኢንተርኘራይዞችን ለእያንዳንዱ 1.4 ሚሊዮን ብር ደጋፍ ተደረገ ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የክልሉን የንብ ሀብት ልማት ለማዘመን እና አናቢውን ተጠቃሚ ለማድረግ በስልጠና፣ በግብዓት አቅርቦትና ድጋፍና ክትትል በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተሰሩ ስራዎችም አበረታች ውጤቶች ተመዝገበዋል፡፡ ጽ/ቤቱ የሚሰራቸው ስራዎች በመደገፍ ኘሮጀክቶች ትልቅ ፋይዳ አላቸው፡፡ከነዚህ ኘሮጀክቶች ውስጥ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ EAAP የተባለ ኘሮጀክት በክልሉ በሚገኙ 6 ወረዳዎች 6 ኢንተርኘራይዞችን ለእያንዳንዱ 1.4 ሚሊዮን ብር በመደገፍ በስልጠና በግብዓት አቅርቦትና መሠረተ ልማቶችን በማሞላት የንብ ሀብት ልማትን ለማዘመን የሚሰራውን ስራ ሲደግፉ ቆይተዋል፡፡ ኘሮጀክቱ የማጠቃለያ ስራ ርክክብ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ 29/03/2014 በዳንግላ ከተማ የመስክ ጉብኝት እንዲሁም በ 30/03/2014 በባህር ዳር ከተማ ኘሮጀክቱ በቆይታው የሰራቸው ስራዎችና በቀጣይ እንዴት ማስቀጠል እንደሚገባ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡ በምክክር መድረኩ የተገኙ ተጠቃሚዎችና ባለድርሻ አካላትም በቀጣይ ስራውን ለማስቀጠል በሚችሉበት ሁኔታ በስፋት ተወያይተው የጋራ መግባባት በማድረግ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
ዜና
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከልን ጎበኙ
ዜና
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሃይለማርያም ከፍያለው የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽቤት ሃላፊ ዶር ጋሻው ሙጨ በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እና የመስክ ምልከታ ላይ የሰጡት አስተያየት
ዜና
በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት የደብረ ዘይት ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዮት የእንስሳት ስነ-ተዋልዶ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ ታምራት ደገፋ በማዕከሉ ተገኝተው የሰጡት አስተያየት
ዜና
የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል ሃላፊ አቶ ፈንታሁን ዳኛው በማዕከሉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አስመልክቱ የሰጡት ማብራሪያ
ዜና
የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ ፡፡
የአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ፣ በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ፣ ከምርምር ተቋማት የመጡ የስራ ሃላፊዎች እና ተመራማሪዎች ፣እንስሳት ሃብት ልማት ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች እና የዘርፉ የዞንና የወረዳ የሚመለከታቸው አመራሮች እና ሙያተኞች በተገኙበት በ24/03/2014 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስተዋወቅ እና ማዕከሉ ከዝርያ ማሻሻል እና መኖ ልማትና ስነ አመጋገብ ከማሻሻል አንጻር የሚሰራቸውን ስራዎች ለተሳታፊዎች የማስጎብኝት ፕሮግራም አካሄደ ፡፡
ዜና
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በእንስሳት ዘርፍ የተሰማሩ የኒዬኖችን በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልላችን በ15 ወረዳዎች በእንስሳት ዘርፍ በ4 እሴት ሰንሰለቶች (ወተት፣ ቀይ ስጋ፣ ዓሳ እና ዶሮ) ላይ ተመሳሳይ ምርት የሚያርቱ አ/አደሮችንና ወጣቶችን በጋራ ፍላጎት ቡድን በማደራጀት 140000 ብር፣ በደረጃ ሁለት በጋራ ፍላጎት ተደራጅተው ትርፍ ምርት በማምረት ላይ የሚገኙትን ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ 1.3 ሚሊዬን ብር እና በከፍተኛ ደረጃ የማቀነባበር ስራ ላይ ለተሰማሩ ዩኒየኖችና ለተሻሻሉ ማህበራት 8.5 ሚሊዬን ብር በመሰረተ ልማት፣ በቁሳቁስ፣ በግብዓትና ስልጠና ድጋፍ በማድረግ የምርትና ምርታማነት በማሳደግ ድጋፍ እያደረገ ይኛል፡፡