ዜና
ለቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት ማዕከል ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጣና ተሰጠ፡፡
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከ29-30/01/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ለቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜትና ጥበቃ ማዕከል ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሄደ ፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኤጀንሲው ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ፈንቴ ቢሻው ሲሆኑ ኃላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው ማዕከሉ የተሻሻሉ ዝርያዎችን እያባዙ ለአርሶ አደሩ በማሰራጨትም ሆነ ንጹህ የፎገራ ዳልጋ ከብት ዝርያዎችን ጠብቆ ከማቆት አንጻር ትልቅ ኃላፊነት የተጣለበት መሆኑን በመግለጽ ይሁን እንጅ ማዕከሉ የተጣለበትን ተግባርና ሃላፊነት በሚፈልገው መጠን አሟልቶ በመፈጸም እረገድ ውስንነቶችን ያሉ መሆኑን ሃላፊው ገልጸው ይህን ስልጠና በሰራተኞች ዘንድ የሚታየውን የክህሎት ክፍተት በመቅረፍ ለቀጣይ ስራ ውጤታማነት አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በስልጠናው ሰልጣኞች የዳልጋ ከብት አያያዝና እንክብካቤ በተመለከተ ከእንስሳት እርባታ እና ጤና አንጻር ሊተኮርባቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶችን በመወያየት ለቀጣይ ስራዎች አቅም የሚሆን ግንዛቤ ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የቻግኒ የዳ/ከብት ዝርያ ማሻሻል እና ብዜት ማዕከል የዝርያ ማሻሻልና ጥበቃ የቀጣይ ተግባራት አቅጣጫ በአቶ አህመድ አልቃድር.pptx
የዳ/ ከብት ጤና አጠባበቅ ዙሪያ ለቻግኒ የብዜት ማዕከል ባለመያዎች እና ተንከባካቤዎች የተዘጋጀ ስልጠና በዶ/ር ታምሩ ተሰማ.pptx
የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ሪፖርት በአቶ ፈንታሁን.pptx
ዜና
የሆርሞን ሲንክሮናይዜሽን ቴክኖሎጂ ውጤታማ ለማድረግ የምንከተላቸው የአሰራር ሞዳሊቲዎች በተመለከተ በአቶ ደመላሽ አይችሌ የተሰጠ ስልጠና ፡፡
ዜና
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የ2013 በጀት ዓመት የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድን ገመገመ፡፡
ኤጀንሲው ከ19-21/1/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ባካሄደው መድረክ የሰሜን ሽዋ፣ ምዕ/ ጐጃም፤ማዕከላዊ ጎንደር እና የኦሮሞ/ብ/አ/ ዞን ተ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች ፤ የወረዳ ተ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ፤ ቡድን መሪዎች እንዲሁም የእርባታ ባለሙያዎችና የአዳቃይ ቴክኒሻኖች በተገኙበት የ2013 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ሰፊ ወይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በውይይቱም በአፈፃፀም ረገድ ክፍተት የሆኑ ችግሮች በተሳታፊዎች በኩል የቀረቡ ሲሆን በኤጀንሲው የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በኩል ይህን ሊፈታ የሚችል ማብራሪያዎችና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በመስራት እና ለቀጣይ ስራ መነቃቃትን በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል፡፡
ዜና
በፎገራ ወረዳ ዓሣን ከእሩዝ ማሳ ጋር አጣምሮ የመከወን የሰራ እንቅስቃሴ ተጎበኝ
የአማራ ክልል የበርካታ ሀይቆች፣ ወንዞች እና ኩሬዎች መገኛ ክልል ነው፡፡ እነዚህ ሀይቆች፣ ወንዞች እና ኩሬዎች ለአሳ ሀብት ልማት ከፍተኛ ጠቀሚታ አላቸው፡፡
ኤጀንሲው ይህን ምቹ ሀብት በመጠቀም የአሳ ሀብት ልማቱን ለማልማት የሚያስችሉ የሰልጠና የግብዓት አቅርቦት እና የድጋፍና ክትትል ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ኤጀንሲው የአሳ እርባታ ስራን ከላይ ከተጠቀሱ የውሃ አካላት በተጨማሪ በአርሶ አደር ደረጃ በተዘጋጀ ኩሬዎችን በሰፋት በማስፋፋት፣ የኬጅ እና ፒን ካልቸር አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን ለተጠቃሚ በማስተዋወቅ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
ዜና
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የ2013 በጀት ዓመት የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድን ገመገመ፡፡
ኤጀንሲው ከ 12-13/1/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ባካሄደው መድረክ የደ/ጐንደር፣ ምስ/ ጐጃም እና የአዊ ዞን ተ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች ፤ የወረዳ ተ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ፤ ቡድን መሪዎች እንዲሁም የእርባታ ባለሙያዎችና የአዳቃይ ቴክኒሻኖች በተገኙበት የ2013 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ሰፊ ወይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በውይይቱም በአፈፃፀም ረገድ ክፍተት የሆኑ ችግሮች በተሳታፊዎች በኩል የቀረቡ ሲሆን በኤጀንሲው የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በኩል ይህን ሊፈታ የሚችል ማብራሪያዎችና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በመስራት እና ለቀጣይ ስራ መነቃቃትን በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል፡፡በድራት ሆርሞን የታገዘ የዳ/ከብቶች ድቀላ.ppt
ዜና
የተሻሻለ የቤተሰብ ደሮ እርባታ የሙከራ ትግበራ የሚተገበርባቸዉ ሞዴል መንደሮች በተመለከተ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ
የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ የተሻሻለ የቤተሰብ ደሮ እርባታ የሙከራ ትግበራ ለሚካሄድባቸዉ ወረዳዎች እና የተመረጡ ሞዴል መንደሮች በተመለከተ የሚመለከታቸዉ አጋር አካላት በተገኙነበት ግንቦት 25/2013 በባህርዳር ከተማ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አካሄደ፡፡
በመድረኩ በግብርና ሚኒስቴር የደሮ እርባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት ወ/ሮ ጽጌረዳ ፍሬዉ የሙከራ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ መነሻ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
ዜና
የቻግኒ የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያና ጥበቃ ማዕከል የ10 ሚሊዮን ብራ ድጋፍ ተደረገለት፡፡
የኢፊድሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ፣ ፣የብሄራዊ ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስራት ቴራ እንዲሁም ከምርምር ፣ ከATA ፣ከLFSDP ፕሮጀክት የመጡ የስራ ሃላፊዎች በ24/09/2013 ዓ.ም ቻግኒ የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያና ጥበቃ ማዕከል የስራ እንቅስቃሴ በመስክ እና በቢሮ ደረጃ ጎበኙ፡፡
ጎብኝዎች በመስክና በቢሮ ደረጃ ከቀረበው ሪፖርት ተነስተው ማዕከሉ ወደ ተሻለ የስራ ደረጃ ሊያሳድጉት በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ወይይት ተደርጓል ፡፡
ዜና
የአለም የወተት ቀን በደማቅ ሁኔታ በአገር አቀፍ ደረጃ በአማራ ክልል ተከበረ፡፡
በአለም ለ21ኛ ጊዜና በኢትዮጵያ ለ5ኛ ጊዜ በፈረንጆች አቆጣጠር በየአመቱ June 1 በሃገራችን ግንቦት 24 የሚከበረው አለም አቀፍ የወተት ቀን “ቀንዎን በአንድ ብርጭቆ ወተት ይጀምሩ” በሚል መሪ ቃል በአማራ ክልል በዳንግላ እና በባህር ዳር ከተማ በመስክ ጉብኝትና በፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡
በበአሉ የኢፊድሪ ግብርና ሚኒስቴር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ፣የብሄራዊ ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስራት ቴራ እና ጥሪ የተደረገለቸው ከክልሎች ፣ ከዩንቨርስቲዎች እና ከምርምር ተቋማት የተገኙ የስራ ሃላፊዎች ፣ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
- የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የ3ኛው ሩብ ዓመት የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀም ገመገመ፡፡
- 31 ማህበራት ከሸማቾች ጋር ለማገናኘት እና በቀጣይ እንዴት ተጋግዘዉ መስራት እንዳለባቸዉ ግንዛቤ የሚፈጥር መድረክ በቀን 09/09/2013 በባህርዳር ከተማ ተካሄደ፡፡
- የምዕራብ አማራ ክፍል ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ ቁጥጥር አሰተባባሪ ከአቶ ኤሌያስ ደምሴ ጋር የተደረገ ቆይታ
- የባ/ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እስመልክቶ ከላብራቶሪ ስራ አስኪያጅ ከአቶ ወንደሰን ቁምላቸው ጋር ያደረግነው ቆይታ