ዜና
የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የ3ኛው ሩብ ዓመት የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀም ገመገመ፡፡
በመድሩኩ የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም በሪፖርት ከመቅረቡ በተጨማሪ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የሆኑ ሴክተር መ/ቤቶች በሩብ አመት ያከናወናቸውን ስራዎች በሪፖርቱ አቅርበዋል ፡፡ በቀረበው ሪፖርት ቤቱ በስፋት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን የቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡
- በሌቭል 1 ደረጃ ያሉ ተጠቃሚዎች ውጤታማ ከማድረግ አንፃር የእንስሳት ሃት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ተቋም ከእርባታ እና ከጤና አንፃር የሚሰሩ ስራዎችን በመለከተ ችግር ፈች ድጋፍ እንዲያደርግ፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክትና ማህበራት በዶሮ እርባታ፣ በቀይ ስጋ ፣ በወተትና በዓሣ ሃብት ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ማህበራት ውጤታማነትን አስመልክቶ ምክክር አካሂደዋል፡፡
የምክክሩ ዓላማ በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት ስራቸውን በእቅድ እንዲመሩ ማስቻል፤ ከሸማቹ የገበያ ትስስር መፍጠር ፣ የተሻለ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ማስቻልና መደገፍ እንደሆነ የአማራ ክልል የኀብረት ስራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ኃላፊ ኃይለልዑል ተስፋ ተናግረዋል፡፡
“አምራችና ሸማች ጥብቅ ትስስር መፍጠራቸው ለሀገር እድገት መሰረት ነው” ያሉት ኃላፊው ሁለቱ አካላት ትስስር የማይፈጥሩ ከሆነ ተጠቃሚ የሚሆነው ሕገ ወጥ ደላላው ብቻ ነው ብለዋል፡፡
ሸማቹ የሚፈልገው የምርት ጥራት ፣አይነት፣ብዛትና ጊዜን በአግባቡ መረዳት አምራቹን ስኬታማ ያደርጋል፤ ለዚህም በየወቅቱ መነጋገር እንደሚያስፈልግ አቶ ኃይለልዑል አስገንዝበዋል፡፡
ዜና
ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች (ፒፒአር) በሽታ ምንነት ፤ መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች እንዲሁም በሽታውን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ የምዕራብ አማራ ክፍል ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ ቁጥጥር አሰተባባሪ ከአቶ ኤሌያስ ደምሴ ጋር የተደረገ ቆይታ
ዜና
የባ/ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እስመልክቶ ከላብራቶሪ ስራ አስኪያጅ ከአቶ ወንደሰን ቁምላቸው ጋር ያደረግነው ቆይታ
ዜና
በሰሜን ጎንደር ዞን አዲ-አርቃ ወረዳ በሳንቅ ብስኒት ቀበሌ ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር) የክትባት አገልግሎት ሲሰጥ
ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር)
ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር) አደገኛ የበጎችና ፍየሎች በሽታ በመባል ይታወቃል፡፡ በጣም አደገኛና በፍጥነት ተዛማችነት ያለው በዋነኝነት ትናንሽ አመንዣኪ የቤትና የዱር እንስሳትን የሚጠቃ ሞርቢሊ ቫይረስ (Morbillivirus) ዝርያ ካለው ከፓራሚኦክሶቫይሪዴይ (Paramixoviridae) አካል የሚመደብ በሽታ ነው፡፡በሽታው በአዲስ መልክ በመንጋ ውስጥ መግባት ከቻለ የመንጋውን ከ50-90% ሊያጠቃ የሚችል ሲሆን በአብዛኛው እስከ 70% እና አንዳንድጊዜ ከዛም በላይ የመግደል አቅም ያለው አደገኛ በሽታ ነው፡፡
ዜና
በአማራ ክልል የተሻለ የእንስሳት ማድለብ ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን እና ባለሃብቶችን ምርጥ ተሞክሮዎችን ለሌሎች ለማሳየት የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር በመተባበር በኤስዲአይ ቮካ ፊድ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ፡፡
ዜና
በአማራ ክልል የተሻለ የዶሮ ሃብት ልማት ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን እና ባለሃብቶችን ምርጥ ተሞክሮዎችን ለሌሎች ለማሳየት የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር በመተባበር በኤስዲአይ ቮካ ፊድ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ፡፡
ዜና
በአማራ ክልል የተሻለ የወተት ሃብት ልማት ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን፤ባለሃብቶችንና አርሶ አደሮችን ምርጥ ተሞክሮዎችን ለሌሎች ለማሳየት የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር በመተባበር በኤስዲአይ ቮካ ፊድ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ፡፡