ዜና
በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በዱርቤቴ ከተማ የሚገኘው ፍቃዱ ዘርፋለምና ጓደኞቻቸው የወተት ላም እርባታ ኢንተርፕራይዝ
ፍቃዱ ዘርፋለምና ጓደኞቻቸው የወተት ላም እርባታ ኢንተርፕራይዝ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ ድርቤቴ ከተማ 5 አባላት በመያዝ በ2010 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን አሁን ላይ ማህበሩ 11 የተሻሻሉ የወተት ላሞችን በመያዝና የተሻሻለ የእንስሳት መኖ በማልማት አርአያነት ያለው ስራ እየሰሩ ይገኛል
ዜና
በአማራ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ፕሮጀክት የደስታ መሰል በሽታ ግብረ ሃይል የ8 ወር አፈጻጸም በግብረ ሃይሉ ተገመገም
በአማራ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ፕሮጀክት የደስታ መሰል በሽታ ግብረ ሃይል በባህርዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ እና በየኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ በ8 ወር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም በግብረ ሃይሉ ተገመገም
ዜና
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የተጠሪ ማዕከላትን የ8 ወር አፈፃፀም በ 26/06/2013 በባህር ዳር ከተማ ገመገመ፡፡
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የተጠሪ ማዕከላትን የ8 ወር አፈፃፀም በ 26/06/2013 በባህር ዳር ከተማ ገመገመ፡፡ ሁሉም ማዕከላት የ8 ወር አፈፃፀማቸወን በሪፖርቱ አቅርበዋል፡፡ ሪፖርቱ ከቀረበ በኃላም በቀረበው ሪፖርት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ በኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ በኩል የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተለይቶ ወይይቱ ተጠናቋል፡፡
ዜና
የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት በ 20/06/2013 ዓም በእንጅባራ ከተማ የ6 ወሩን የኘሮጀክት አፈፃፀም በቴክኒክ ኮሚቴው ተገመገመ፡፡
የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት በ 20/06/2013 ዓም በእንጅባራ ከተማ የ6 ወሩን የኘሮጀክት አፈፃፀም በቴክኒክ ኮሚቴው ገመገመ፡፡ የኘሮክቱ የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም በኘሮጀክቱ በኩል ከቀረበ በኃላ ከቤቱ በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ በስፋት ተወያያቶ የሚከተሉትን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡
ዜና
ከአሁን በፊት በቆሎ እና ዳጉሳ ይዘሩበት የነበረውን ማሳቸውን የተሻሻለ የእንስሳት መኖ በመዝራት በወተት ሃብት ልማት ስራ ተጠቃሚ የሆኑት አርሶ አደር ተሾመ መለስ
በምዕራብ ጎጃም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ አብችክሊ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ተሾመ መለስ ከአሁን በፊት በቆሎና ዳጉሳ ይዘሩት የነበረውን ማሳቸውን እንዲሁም ከግለሰቦች የማሳ መሬቶችን በመከራየት በ1.5 ሄክታር የተሻሻለ የእንስሳት መኖ በመዝራት በ2008ዓ.ም በወተት ሃብት ልማት ስራ የገቡ ሲሆን አርሶ አደሩ አሁን ላይ 7 የወተት ላሞች እና 5 ጥጆች ያሎቸው ሲሆን በቀን ከ52 ሊትር በላይ ወተት እንደሚያገኙ ገልጸውልናል ፡፡
ዜና
የፌደራል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ እና የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ዙሪያ የሰጡት አስተያየት ፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ ከጥር 17-21/2013 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲያካሄድ፡፡በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ተካፋይ የነበሩት ከአማራ ክልል ህብረት ስራ ኤጀንሲ እና ከአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የመጡ ባለሙያዎች እና የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የወረዳ አስተባባሪዎች በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ዙሪያ የሰጡት አስተያየት
- የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲያካሄድ፡፡
- በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡
- በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ከአረብ ሃገር ተመልሰው በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተደራጁት ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይ
- በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከአረብ ሃገር ተመልሳ በወተት ሃብት ልማት ስራ የተሰማራችው ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን በ2010 ዓ.ም 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገባች ሲሆን አሁን ላይ በቀን ከ650 ብር ያላነሰ ከወተት ሽያጭ ታገኛለች፡፡