ዜና
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲያካሄድ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ
1 በገቨርናንስና ንዑስ ፕሮጀክት አዘገጃጀት
2 በአካባቢ እና ማህበራዊ ደህንነት ጉዳይ
3 በግብይት ሰንሰለት ዙሪያ ከጥር 17-21/2013 በእንጅባራ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና አካሄደ፡፡
ዜና
በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚሰራቸው በርካታ ስራዎች ውስጥ ወጣቶች በዘርፉ በስፋት ተደራጀተው እንዲገቡ እና የተሻለ አሰራር ተከትለው እንዲሰሩ ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡ በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡ኢንተርኘራይዙ የሚገኝው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ላስታ ገራዶ 04 ቀበሌ ሲሆን ስራ የጀመረው በ2007 ዓም በ 5 ላሞች ነው፡፡
ዜና
በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ከአረብ ሃገር ተመልሰው በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተደራጁት ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይ በ2009 ዓም 1000 ጫጩቶችን በመያዝ ስራ የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ በዓመት ከ20,000 ያላነሱ ጫጩቶችን በማሳደግ ለተጠቃሚዎች ያቀርባሉ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ህ/ሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከስራቸው ስራዎች አንዱ የተሻለ የእንቁላል እና የስጋ መጠን የሚሰጡ የዶሮ ዝርያዎችን በግብዓት አቅራቢዎች አማካኝነት ለህብረተሰብ እንዲዳረስ እና ሳይንሳዊ አሰራሩን ተከተለው እንዲሰሩ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡ ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይዝ የሚገኝው በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ሲሆን ኢንተርኘራይዙ በ2009 ዓም 1000 ጫጩቶችን በማሳደግ ስራ የጀመረ ሲሆን
ዜና
በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከአረብ ሃገር ተመልሳ በወተት ሃብት ልማት ስራ የተሰማራችው ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን በ2010 ዓ.ም 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገባች ሲሆን አሁን ላይ በቀን ከ650 ብር ያላነሰ ከወተት ሽያጭ ታገኛለች፡፡
የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በውስን ካፓታል እና መሬት ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ ነው፡፡ በዘርፉ በርካታ ወጣቶች እና ሴቶች ወደ ስራ በመግባት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ወጣቶችና ሴቶች መካከለ ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን አንዳ ናት፡፡ ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን ነዋሪነቷ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ሲሆን ግለሰቧ የወተት ሀብት ልማት ስራ የጀመረችው በ2010 ዓም ነው፡፡ አሁን ላይ 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ እና ባላት ውስን ቦታ የተሻሻሉ የመኖ ልማቶችን በማልማትና
ዜና
በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በወተት ሃብት ልማት ስራ የተሰማራው ወጣት ናስር ሙህመድ 9 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራው ገብቶል
የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በውስን ካፓታል እና መሬት ለወጣቶችና የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ ነው፡፡ በዘርፉ በርካታ ወጣቶች ወደ ስራ በመግባት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ወጣቶች መካከለ ናስር ሙህመድ አንዱ ነው ወጣት ናስር ሙህመድ ነዋሪነቱ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆን ግለሰቡ የወተት ሀብት ልማት ስራ የጀመረችው በ2010 ዓም ነው፡፡ አሁን ላይ 9 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራው በመግባት በመርሳ ከተማ የወተት ተዋፅኦዎችን ለአካባቢው ማህበረሰብ እያቀረበ ይገኛል በዚህን ተጠቃሚ መሆኑን ገልጾልናል፡፡
ዜና
በአዊ ብ/አ/ዞን በእንጅባራ ከተማ በወተት ሃብት ልማት ሰራ የተሰማሩት አለም የወተት ላም እርባታ 18 ላሞች፣ ጊደሮች እና ጥጆች በመያዝ በዘርፉ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል፡፡
በአማራ ክልል ከሚገኝ በርካታ የወተት ላም እርባታ ድርጅቶች አንዱ አለም የወተት ላም እርባታ ነው፡፡ የወተት ላም እርባታው የሚገኝው በአዊ ብ/አ/ዞን በእንጅባራ ከተማ ነው፡፡ የወተት ላም እርባታው በ 2003 ዓ.ም እንደጀመረ የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ የሽወርቅ ምህረት ገልፀውልናል፡፡የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ የሽወርቅ ምህረት አሁን ላይ በእርባታ ድርጅቱ ቁጥራቸው ከ 18 ያላነሱ ላሞች፣ ጊደሮች እና ጥጆች እንደሚገኙ ጠቁመው በቀን ከ 80 ሊትር ያላነሰ ወተት እንደሚያገኙና በዚህም ሂውታቸውን በተሻለ መልኩ እየመሩ እንደሆነ ገልፃዋል፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንሰሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከፋርም ሬዲዮ ጋር በመተባበር
በዶሮ እርባታ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በዶሮ ዙርያ አስተማሪ የሆኑ መልእክቶችን
በአማራ ሬዲዮ ዘወትር እሮብ ማታ ከ1፡20 እስከ 1፡50 እንዲሁም በድጋሜ እሁድ ከቀኑ
ከ11:20 እስከ 11:50 ያስተላልፋል።በመሆኑም ፕሮግራሙን በመከታተል አስተያየታችሁን
እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ዜና
በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች የስራ እንቅስቃሲ
የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰንቶ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የተሻለ የእንቁላል ምርትና ስጋ መስጠት የሚችሉ የውጭ ደም ያላቸው የዶሮ ዝርያዎች ከ 1 ቀን ጫጩት አቅራቢ ካምፓኒዎች አሳዳጊዎች እየወሰዱ እንሚያሳደጉ አስፈላጊ ሙያዊ እገዛዎችን በቅድመ ዝግጅትና በተግባር ምዕራፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ኤጀንሲው በ2012 በጀት አመት በ 1 ቀን ጫጩት ማሳደግ ስራ በሰራ ላይ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው በኢንተርኘራይዝ የተደራጅ አሳዳጊዎች ቁጥር 2250 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 754 ሴቶች ናቸው፡፡