በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ በይካቲት ወር የሚዲያ ሽፋን ያገኙ ስራዎች
ዜና
የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በደረጃ ሶስት ተጠቃሚ ከሆኑ 5 ስፒሻላይዝድ ኮፕሬቲቭ እና ዩኔኖች ጋር ፕሮጀክቱ በሚያደርግላቸው ድጋፍ እና ከፕሮጀክቱ ድጋፍ በፊት በቅድመ ዝግጅት መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ ፡፡
በመድረኩ የክልል፣የዞን እና የወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት ፣ የህብረት ስራ ማስፋፊያ ተ/ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የ5 ስፒሻላይዝድ ኮፕሬቲቭ እና ዩኔኖች የሰራ ኃላፊዎች እና ከንግድና ገበያ ልማት ተቋም የመጡ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ፡፡
በመድረኩ ለመነሻ የሚሆን የመወያያ ጹሁፍ በፕሮጀክቱ በኩል ቀርቦል ፡፡ በቀረበው የመነሻ ጹሁፍ መነሻ በማድረግ ከማህበራት እና ከዩኔኖች የመጡ ተወካዮች ሀሳብ ሰጥተዋል ፡፡
በተጨማሪም በየደረጀው ያሉ ከእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት ፣ ከህብረት ስራ ማስፋፊያ ተ/ጽ/ቤት እና ከንግድና ገበያ ልማት የመጡ የስራ ኃላፊዎች እና ሙያተኞች
ዜና
በምስራቅ አማራ በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ በጋራ ፍላጎት ቡድን የተደራጅ ተጠቃሚዎችን ወደ ህብረት ስራ ማህበር ለማሳደግ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ ፡፡
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በምስራቅ አማራ ድጋፍ በሚያድረግባቸው ስድስት ወረዳዎች ደሴ ዙሪያ ወረዳ ፣ ቃሉ ወረዳ ፣ ጉባላፍቶ ወረዳ ፣ ዳዋጨፋ ወረዳ ፣ ሞረትና ጅሩ ወረዳ እና ባሶናወረና ወረዳ በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ተደራጁ ለሚገኙ 40 (አርባ) የህብረት ስራ ማህበር አባላትና አመራሮች ፣ የህብረት ስራ ማህበራት ገዥዎች ፣ የወረዳ ፕሮጅክት አሰተባባሪዎች ፣ የወረዳ እና የክልል የህብረት ስራ ማስፋፊያ ባለሙያዎች ፣ የእንስሳት እና ዓሳ ልማት ጽ/ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት የግንዛቤ ፍጠራ መድረክ አካሄደ፡፡
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች በደረጃ አንድ (በጋራ ፍላጎት ቡድን) ተደራጅተው ሲሰሩ የቆዩትን በአዲስ መልክ ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ እና በደረጃ አንድ ተጠቃሚ የነበሩትን ወደ ነባር ህብረት ስራ ማህበራት እንዲገቡ በማስቻል በ2015 ዓ/ም 112 ህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት በፕሮጀክቱ የተቀመጡትን መስፈርቶች በመከተልና በማወዳደር 70 የህብረት ስራ ማህበራትን ለእያንዳንዳቸው 1,580,000 ብር በድምሩ 110,600,000.00 ብር ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡:
ዜና
በምዕራብ አማራ በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ በጋራ ፍላጎት ቡድን የተደራጅተው ተጠቃሚዎችን ወደ ህብረት ስራ ማህበር ለማሳደግ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ ::
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ተደራጁ ለሚገኙ 67 (ስልሳ ሰባት) የህብረት ስራ ማህበር አባላትና አመራሮች ፣ የወረዳ እና የክልል የህብረት ስራ ማስፋፊያ ባለሙያዎች ፣ የእንስሳት እና ዓሳ ልማት ጽ/ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት የግንዛቤ ፍጠራ መድረክ አካሄደ፡፡
የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች በደረጃ አንድ (በጋራ ፍላጎት ቡድን) ተደራጅተው ሲሰሩ የቆዩትን በአዲስ መልክ ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ እና በደረጃ አንድ ተጠቃሚ የነበሩትን ወደ ነባር ህብረት ስራ ማህበራት እንዲገቡ በማስቻል በ2015 ዓ/ም 112 ህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት በፕሮጀክቱ የተቀመጡትን መስፈርቶች በመከተልና በማወዳደር 70 የህብረት ስራ ማህበራትን ለእያንዳንዳቸው 1,580,000 ብር በድምሩ 110,600,000.00 ብር ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡
በምስራቅ አማራ ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ በመከላከል ረገድ የተሰሩ ሰራዎችን በተመለከተ ከአቶ ንጉሴ ተፈራ የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርመራ ዳይሬክተር ጋር የተደረገ ቆይታ
ዜና
በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ አውዘት ቀበሌ አለቅት ወንዝ ፍጋን ተብሎ የሚጠራው ተፋሰስ የለማ የውል የግጦሽ መሬት እና የዝርያ ማሻሻል ስራ ተጎበኘ ::